የኦንላይን ድር ድጋፍ
ለተጨማሪ ድጋፍ ፣ ዝመናዎች ፣ ፊርምዌር ፣ ዳውንሎዶች እና አጋዥ ስልጠናዎች ይህንን ይጎብኙ፥www.sony-mea.com/en/electronics/support
የእውቂያ ማዕከል
ባለሙያዎቻችን ፈጣን መፍትሄዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ እዚህ ይገኛሉ።
የቴክኒክ ድጋፍ እና ጥገናዎች
ከዚህ በታች ባለው የአገልግሎት ማእከል ማንኛውንም ቴክኒካዊ ችግር የሚፈቱላቸው የእኛን መሐንዲሶችን ያግኙ
የ Sony ምርት ስለገዙ እናመሰግናለን።
እባክዎ የዋስትና ደምቦችን እና ሁኔታዎችን በተመለከተ ከዚህ በታች ይመልከቱ
Sony የመካከለኛው ምስራቅ እና የአፍሪካ FZE (“እኛ”, “Sony”) ለ Sony ምርቶች በክፍል (1) እስከ (4) እንደተመለከተው የአምራች የዋስትና ሽፋን ያቀርብልዎታል (“የአምራች ዋስትና”)።
እባክዎ ከዚህ በታች የቀረበውን የዋስትና ማረጋገጫ ደምቦች እና ሁኔታዎች በጥንቃቄ ያንብቡ እና ይረዱ።
የአምራች የዋስትና ማረጋገጫ ደምቦች እና ሁኔታዎች፥
1) በአምራች የዋስትና ማረጋገጫ ስር ሽፋን ያላቸው የ Sony ምርቶች፥
የ Sony ምርት ከዚህ በታች እንደተዘረዘረው የ Sony ብራንድ ምርቶች ማለት ሲሆኑ፣ እርስዎ እንደ ደንበኛ የገዟቸው፣ ይህም የግዢውን ቀን ፣ የምርቱን የሞዴል ስም ፣ የቸርቻሪው ስም/ማህተም የሚያመለክት፣ ትክክለኛ የሆነ የግዥ ማረጋገጫ (የመጀመሪያ የክፍያ መጠየቂያ ወይም የሽያጭ ደረሰኝ) ያላቸው ማለት ነው።
በዋስትና ሽፋን ያላቸው የ Sony ምርቶች | የዋስትና ጊዜ |
---|---|
ቴሌቪዥኖች | 1 ዓመት |
DVD እና BD ማጫወቻ | 1 ዓመት |
የቤት ትያትር | 1 ዓመት |
HiFi ኦዲዮ ሲስተም | 1 ዓመት |
HiFi ክፍለ አካል | 1 ዓመት |
ሬዲዮ ካሴት | 1 ዓመት |
ሬዲዮ | 1 ዓመት |
ዲጂታል የሙዚቃ ማጫወቻ | 1 ዓመት |
IC ድምጽ መቅጃ | 1 ዓመት |
ገመድ ኣልባ ስፒከር | 1 ዓመት |
ሄድፎን (የብሉቱዝ ሞዴሎች ብቻ) | 1 ዓመት |
የመኪና ድምጽ | 1 ዓመት |
የሚለዋወጥ ሌንስ ካሜራ | 1 ዓመት |
የሚለዋወጥ ሌንስ | 1 ዓመት |
ዲጂታል የታመቀ ካሜራ | 1 ዓመት |
ካምኮርደር እና የኣክሽን ካሜራ | 1 ዓመት |
ከላይ በተዘረዘረው ውስጥ የሌሉት ምርቶች፣ በአምራች ዋስትና ሽፋን ያልተሰጣቸው ናቸው እና የዋስትና መረጃውን ለማግኘት እባክዎ የአከባቢዎን ቸርቻሪ ያነጋግሩ።
2) በአምራች የዋስትና ማረጋገጫ ስር ሽፋን የሌላቸው ዕቃዎች፥
(i) መለዋወጫዎች (እንደ ሪሞት ፣ አዳፕተሮች ፣ ኬብሎች እና ተመሳሳይ ዕቃዎች ያሉ)
(ii) አላቂ እቃዎች (እንደ ባትሪ እና ተመሳሳይ ዕቃዎች ባሉ በምርት ዕድሜ ውስጥ በየጊዜው መተካት ይፈልጋሉ ተብለው የሚታሰቡ ክፍሎች)
(iii) የምርቱ መዋቢያ አካላት (እንደ ካቢኔቶች ፣ ቁልፎች ፣ ማብሪያ ማጥፊያዎች እና ተመሳሳይ ዕቃዎች ያሉ)
(iv) ሶፍትዌር እና ማንኛውም ማዘመኛዎች
3) የአምራች የዋስትና ሁኔታዎች፥
ሀ) ከአምራች ዋስትና ተጠቃሚ ለመሆን፣ የ Sony ምርትን የገዙበትን ቀን የሚያሳይ የተፈቀደለት የሻጩን የክፍያ መጠየቂያ ወረቀት/ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርብዎታል።
ለ) የቀረበው የአምራች ዋስትና፣ የተጠቀሰውን የ Sony ምርት ለመጠገን ብቻ ነው እንጂ፣ የምርቱን ምትክ ለማቅረብ ኣይደለም፣ ወዘተ።
ሐ) የቀረበው የአምራች ዋስትና ለሚከተሉት ሽፋን አይሰጥም፥
- ከ እና ወደ አገልግሎት ማእከል መጓጓዝ ፣ የመርከብ ወጪ ፣ የአገር ውስጥ ግብር እና ሌሎች ሊከሰቱ የሚችሉ ከትራፊክ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ወጪዎች።
- የአንድን እቃ የማስወገድ እና የመጫን/የመትከል።
- ማንኛውም የምርቱ አካላዊ ጉዳት ወይም ከልክ በላይ ሙቀት በመኖሩ ምክንያት የተቃጠለ አካላት፣ በእርጥበት ፣ ፈሳሽ ፣ ነፍሳት ፣ የውጭ ነዳጆች ፣ምክንያት መበስበስ/መዛግ ፣ የውስጥ የመስታወት መሰበር ፣ አደጋዎች ፣ የመጓጓዣ ጉዳት ፣ የኃይል መለዋወጥ ፣ የምርት አላግባብ መጠቀም ፣ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ማጽዳት ፣ ማርጀት እና መቀደድ ፣ የተፈጥሮ አደጋ ፣ የፈጣሪ ስራ ፣ እና ወይም የአጠቃቀም መመሪያዎችን የሚጥስ ወይም በእነዚህ መመሪያዎች ውስጥ ያልተካተተ ማንኛውም ክዋኔ።
- በ Sony ፈቃድ ባልተሰጠው ማንኛውም ሰው የተነካኩ ወይም ጥገና የተደረገላቸው የ Sony ምርቶች።
- የ Sony ምርቶች ፣ የሞዴል ስማቸው ወይም መለያ ቁጥራቸው ከተጠቀሰው ጥቅል ፣ የክፍያ መጠየቂያ / ደረሰኝ ፣ ወይም በምርቱ ካርቶን ላይ ካለው ፣ ጋር የማይዛመድ፣ ወይም ከተቀየሩ/ከተለወጡ ፣ ከተወገዱ ወይም ሆን ተብሎ ጉዳት ከደረሰባቸው።
መ) የአምራቹ የዋስትና ማረጋገጫ ከላይ በተጠቀሱት ሁኔታዎች ስር ተፈፃሚነት ዮረዋል ወይም አይኖረውም ብለው ሊፈርዱ የሚችሉት፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በ Sony ፈቃድ የተሰጣቸው የአገልግሎት ማዕከላት ብቻ ናቸው።
4) ማስተባበያ፥
በሚመለከታቸው ህጎች እስከሚፈቅደው ድረስ፣ በ Sony ምርቶች ላይ ተፈፃሚነት ያለው ዋስትና አይኖርም (የጥራት አጥጋቢነት ወይም ለተወሰነ ዓላማ ብቁነትን ጨምሮ)። በአምራቹ የዋስትና ማረጋገጫ በተገለፁ መንገዶች ብቻ፣ መብትዎን ማስከበር ወይም በእርስዎ ላይ የደረሰውን ማንኛውንም ጉዳት ማዳን ይችላሉ። Sony፣ በውል ፣ በማጭበርበር ፣ ወይም በሌላ መልኩ በመመርኮዝ ከ Sony ምርቶች ወይም ከነዚህ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ፣ የውሂብ መጥፋት ወይም በድንገት ፣ በተዘዋዋሪ ፣ በልዩ ሁኔታ ወይም ተያያዥ በሆኑ ጉዳቶች ምክንያት (ጥቅማጥቅሞችን ወይም ትርፎችን ማጣትንም ጨምሮ) ተጠያቂ አይሆንም።
የአምራች ዋስትና ለመጠቀም እባክዎ የሚከተለውን ፈቃድ ያለው የ Sony የአገልግሎት ማእከል ያነጋግሩ፥
ግሎርየስ ኅላ.የተ.የግል ኩባ.
ማህተማ ጋንዲ መንገድ 1ኛ ወለል ሳሙኤል ደረሳ ህንጻ ፒያሳ ከላየን ፋርማሲ ኣጠገብ አዲስ አባባ። ኢትዮጵያ
ስልክ፥
+251 111570013
+251 111570261
ኢሜይል፥ service@glorious-plc.com
የአገልግሎት ሰዓታት፥
ከሰኞ-ሓሙስ; 08:00am - 12:30pm / 02:00pm - 05:30pm
ዓርብ; 08:00am - 11:30am / 02:00pm - 05:30pm
ቅዳሜ; 08:00am - 12:30 pm